ሰንደቅ ዓላማ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ሰንደቅ ዓላማ
Remove ads

|የእስራኤል ሰንደቅ ዓላማ]] ሰንደቅ ዓላማ በቋሚ ላይ እንዲውለበለብ የሚሰቀል ጨርቅ ነው። በድሮ ጊዜ መረጃ መለዋወጥ ዋነኛ ጥቅሙ ነበረ። በአሁኑ ጊዜ ግን የአንድን ሀገር ወይም ድርጅት ለመወከል ያገለግላል።

Thumb

አቶ ከበደ ሚካኤል "ታሪክና ምሳሌ - ፩ኛ መጽሐፍ" በተባለው ድርሰታቸው ላይ፦ ሰንደቅ ዓላም የነጻነት ምልክት የአንድ ሕዝብ ማተብ፤ የኅብረት ማሰሪያ ጥብቅ ሐረግ ነው። «ተመልከት ዓላማህን፣ ተከተል አለቃህን።» ብለው አስፍረውታል።

«ሰንደቅ» የሚለው ቃል ከቱርክኛ «ሳንጃክ» ደረሰ። በኦቶማን ቱርክ ዘመን ይህም ከ«አላማ ሰንደቅ» በላይ «አስተዳደር ክልል» አመለከተ፣ ለምሳሌ የኖቪባዛር ሳንጃክ በዛሬው ሰርቢያ ዙሪያ እስካሁን «ሳንጃክ» ተብሏል።

እንዲሁም «ባንዲራ» የሚለው ቃል ከጣልኛ «ባንዲየራ» የአድዋ ጦርነት በኋላ ደረሰ። እሱና በሌሎች አውሮፓዊ ቋንቋዎች ተመሳሳይ ቃላት የመጡ ከቅድመ-ጀርማኒክ *ባንድ «ማሠርያ፣ ጥብጣብ» ነበር።

Remove ads

ሌሎች መጣጥፎች

የዓለም ባንዲራዎች

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads