ሶበክነፈሩ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ሶበክነፈሩ
Remove ads

ሶበክነፈሩ (ወይም ነፈሩሶበክ) ግብጽን በመካከለኛ መንግሥት (12ኛው ሥርወ መንግሥት) መጨረሻ ከ1823 እስከ 1819 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛች ሴት ፈርዖን (ንግስት) ነበረች። የወንድሟ 4 አመነምሃት ተከታይ ነበረች።

==

Quick facts ሶበክነፈሩ, ግዛት ...

==

የተገኙት ሐውልቶቿ ሁሉ ራሳቸውን ያጡ ናቸው። የቶሪኖ ቀኖና በተባለው ፈርዖኖች ዝርዝር መሠረት ሶበክነፈሩ ለ፫ ዓመታት፣ ፲ ወርና ፳፬ ቀን ነገሠች።

የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት እንደሚያስበው፣ በእርሷ ዘመን (በ1821 ዓክልበ. ግ.) የ14ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያ ፈርዖን ያክቢም ሰኻኤንሬአባይ ወንዝ አፍ ዙሪያ ለእርሷ ተገዥ ሆኖ ነገሠ። እነዚህ ከከነዓን የደረሱ ሴማዊ እረኞችና ነጋዴዎች ነበሩ። በጤቤስ ፈርዖኖች ፈቃድና ስምምነት ግዛታቸው በስሜን ግብጽ የንግድ ማዕከል ሆነ፤ ይህም በብሉይ ኪዳን ጌሤም የተባለው ሀገር ነው።

13ኛው ሥርወ መንግሥት በጤቤስ ተከተላት፤ የዚህም መጀመርያ ፈርዖን አሁን ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ እንደ ነበር ይታመናል። ግብጽ እንደገና ተከፋፍሎ የመካከለኛው መንግሥት መጨረሻ እና የ፪ኛው ጨለማ ዘመን መጀመርያ ይቆጠራል።

ቀዳሚው
4 አመነምሃት
ግብፅ ፈርዖን ተከታይ
ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ
Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads