ቡሩንዲ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ቡሩንዲ
Remove ads

የቡሪንዲ ሪፕብሊከ (ቀድሞ ኡሩንዲ (urundi) የተባለ ሲሆን) በአፍሪካ ውስጥ የምትግኝ ተንሽ አገር ናት። በሩዋንዳታንዛኒያ፥ እና በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ትዋሰናልች። አገሯ ወደብ-የለሽ ብትሆንም ከታንጋንዪካ ሐይቅ ጋር ትዋሰናለች። የቡሩንዲ ዋና ከተማ እስከ ታህሳስ 2011 ዓም ድረስ ቡጁምቡራ ሲሆን ከዚያ ወደ ጊቴጋ ተዛወረ። የሀገሩ የህዝብ ብዛት ወደ 8.7 ሚሊዮን እንደሆነ ይገመታል።

Quick facts Republika y'u Burundi République du Burundi የቡሩንዲ ሪፐብሊከ ...

ቱዋቱትሲሁቱ ብሔሮች በቡሩንዲ ለአምስት ምእተ ዓመታት ያህል ኖረዋል። የቱትሲ ሕዝብ ቡሩንዲን በየንጉሥ መንግሥትነት ለሁለት መቶ ዓመታት ያህል መርቷል። ግን በ፳ኛው ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ፣ አካባቢው በጀርመንቤልጅግ ቁጥጥር ስር ላይ ኖሯል። ቡሩንዲና ሩዋንዳም አንድ ላይ ሩዋንዳ ኡሩንዲ እየተባሉ በቅኝ ግዛት ጊዜ ተጠርተዋል።

በአካባቢው የሰፈነው የፖለቲካ ቀውስ በቡሩንዲ የእርስ በርስ ጦርነት ፈጥሮአል። በአሁኑ ጊዜ ቡሩንዲ ፕሬዝዳንታዊ የተወካዮች ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሆና ትመራለች። ከሀገሩ ሕዝብ ውስጥ ፷፪ ከመቶ የሮማ ካቶሊክ እምነት ተከታይና ከ፰ እስከ ፱ ከመቶ እስላም ሲሆን የተቀረው ሌሎች የክርስትና ዕምነቶችን ወይም ባህላዊ ሃይማኖቶችን ይከተላል።

ቡሩንዲ ከዓለም አስር እጅግ ድሀ ሀገራት አንዷ ናት። የዚህ ምክንያት ከሆኑት ውስጥ ጦርነቶች፣ ሙስና፣ የትምህርት አለመስፋፋትና የኤድስ በሽታ ይጠቀሳሉ። የተፈጥሮ ሀብቶቿ መዳብኮባልትን ይጨምራሉ። ኤክስፖርት ከምታደርጋቸው ምርቶች መካከል ዋናዎቹ ቡናስኳር ናቸው።

Remove ads

ታሪክ

የመጀመሪያው የቡሩንዲ ነዋሪዎች የፒግሚ ሰዎች ናቸው። ከዛም በባንቱ ሕዝቦች ባብዛኛው ተተክተዋል። በ16ኛው ክፍለ ዘመን ነጻ መንግሥት ነበረ። ከዛ በ1903 እ.ኤ.አ.ጀርመን ቅኝ ግዛት ሆነች። በአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ወደ ቤልጅግ ተላለፈች።


Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads