ኤራ-ኢሚቲ
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ኤራ-ኢሚቲ በሱመር የኢሲን ሥርወ መንግሥት ፱ኛው ንጉሥ ነበረ (1780-1772 ዓክልበ. የነገሠ)። የሊፒት-ኤንሊል ልጅና ተከታይ ነበረ።
በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ ፰ ዓመታት እንደ ነገሠ ሲለን፣ ፯ ዓመት ስሞች ያህል ይታወቃሉ።[1]
- 1 - «ኤራ-ኤሚቲ ንጉሥ የሆነበት ዓመት» (1780 ዓክልበ. ግ.)
- a - «ፍትሕ የመሠረተበት ዓመት»
- b - «ኒፑርን ወደሚገባው ሥፍራ የመለሰበት ዓመት»
- c - «ኒፑርን ወደሚገባው ሥፍራ ከመለሰበት ዓመት በኋላ የሆነው ዓመት»
- d - «ኪሡራን የያዘበት ዓመት» (1776 ዓክልበ. ግ.)
- e - «የካዛሉ ግድግዳ የጠፋበት ዓመት»
- f - «የኤራ-ኢሚቲ ከተማ ግድግዳ የሠራበት ዓመት»
በተጨማሪ «የቀድሞ ነገሥታት ዜና መዋዕል» የሚባለው ጽላት ስለ ኤራ-ኢሚቲ እንዲህ ይላል፦
- «ንጉሡ ኤራ-ኢሚቲ የአጸድ ጠባቂውን ኤንሊል-ባኒን እንደ (ጊዜያዊ) ምትኩ ሾመው፤ ንጉሣዊ ዘውዱንም በራሱ ላይ አጫነው። ኤራ-ኢሚቲ ትኩስ ሾርባ እየዋጠ እቤተ መንግሥት ሞተ። በዙፋኑ የተቀመጠው ኤንሊል-ባኒ አልተወውም፤ ለንጉሥነቱ ተሾመና።»[2]
ቀዳሚው ሊፒት-ኤንሊል |
የኢሲን ንጉሥ 1780-1772 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ኤንሊል-ባኒ |
Remove ads
ዋቢ ምንጮች
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads