ኤራ-ኢሚቲ

From Wikipedia, the free encyclopedia

Remove ads

ኤራ-ኢሚቲሱመርኢሲን ሥርወ መንግሥት ፱ኛው ንጉሥ ነበረ (1780-1772 ዓክልበ. የነገሠ)። የሊፒት-ኤንሊል ልጅና ተከታይ ነበረ።

ሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ላይ ፰ ዓመታት እንደ ነገሠ ሲለን፣ ፯ ዓመት ስሞች ያህል ይታወቃሉ።[1]

1 - «ኤራ-ኤሚቲ ንጉሥ የሆነበት ዓመት» (1780 ዓክልበ. ግ.)
a - «ፍትሕ የመሠረተበት ዓመት»
b - «ኒፑርን ወደሚገባው ሥፍራ የመለሰበት ዓመት»
c - «ኒፑርን ወደሚገባው ሥፍራ ከመለሰበት ዓመት በኋላ የሆነው ዓመት»
d - «ኪሡራን የያዘበት ዓመት» (1776 ዓክልበ. ግ.)
e - «የካዛሉ ግድግዳ የጠፋበት ዓመት»
f - «የኤራ-ኢሚቲ ከተማ ግድግዳ የሠራበት ዓመት»

በተጨማሪ «የቀድሞ ነገሥታት ዜና መዋዕል» የሚባለው ጽላት ስለ ኤራ-ኢሚቲ እንዲህ ይላል፦

«ንጉሡ ኤራ-ኢሚቲ የአጸድ ጠባቂውን ኤንሊል-ባኒን እንደ (ጊዜያዊ) ምትኩ ሾመው፤ ንጉሣዊ ዘውዱንም በራሱ ላይ አጫነው። ኤራ-ኢሚቲ ትኩስ ሾርባ እየዋጠ እቤተ መንግሥት ሞተ። በዙፋኑ የተቀመጠው ኤንሊል-ባኒ አልተወውም፤ ለንጉሥነቱ ተሾመና።»[2]
ቀዳሚው
ሊፒት-ኤንሊል
ኢሲን ንጉሥ
1780-1772 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኤንሊል-ባኒ
Remove ads

ዋቢ ምንጮች

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads