ገላውዴዎስ
የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ከ1540 እስከ 1559 ዓ.ም From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ዓፄ ገላውዴዎስ ከጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፭፻፴፫ ዓ/ም እስከ መጋቢት ፳፯ ቀን ፲፭፻፶፩ ዓ/ም ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። ግዛታቸው በኢትዮጵያና አዳል ጦርነት ጊዜ ነበር። ዓፄ ገላውዴዎስ የስቅለተ ዓርብ ዕለት በአዋሽ አካባቢ ከአዳሉ አሚር ኑር ጋር በተደረገው ጦርነት ላይ ተወግተው ሞቱ። በዚሁ ጦርነት ላይ የደብረ ሊባኖስ እጨጌ ዮሐንስም ሕይወታቸውን አጥተዋል። የታሪኩ ምሑር ሪቻርድ ፓንክኸርስት፣ አሚር ኑር የንጉሠ ነገሥቱን ጭንቅላት ወደይፋቱ ሡልጣን ሳዳዲን እንደላከው ለመረጃ የሐረርን ዜና መዋዕል ይጠቅሳሉ።
==
==
Remove ads
ዋቢ ምንጮች
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ)Richard K. P. Pankhurst. The Ethiopian Royal Chronicles. Addis Ababa: Oxford University Press, 1967.
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads