ፑንት
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ፑንት (ፕወነት)[1] ከጥንታዊ ግብጽ ጋራ ንግድ ያካሄድ የነበረ ሀገር ነበር። ግብጻዊ ተጓዦችና መርከበኞች ከዚያ ወርቅ፣ ሙጫ፣ ቆጲ፣ የዝሆን ጥርስ፣ ባርያዎችና አውሬዎች ያመጡ ነበር። ፑንት ደግሞ አንዳንዴ «ታ ነጨር» (ሀገረ አምላክ) ይባላል።[2]

ፑንት በቀይ ባሕር ዳርቻ ወይም በአፍሪቃ ወገን[3] ወይም በአረቢያ ወገን[4]ወይም ምናልባት በሁለቱም እንደ ተገኘ ይታሰባል።
በአንዳንድ ዘመናዊ መምህሮች ዘንድ ፑንት ከፉጥ (የካም ልጅ) ጋር መታወቂያ ሊኖረው ይችላል።[5]በተለመደው ልማድ ግን ይህ ፉጥ በቀይ ባሕር አካባቢ ሳይሆን በሊብያ ነበር የሠፈረው።
የግብጽ ግንኙነት ከፑንት ጋር

- 2003 ዓክልበ. ግድም - የ3 መንቱሆተፕ አለቃ ሃኑ የፑንት ጉዞ መራ።[7]
- በ1 ሰኑስረትና 2 አመነምሃት ዘመኖች (1972-1905 ዓክልበ.) ደግሞ ጉዞዎች ወደ ፑንት ሄዱ።[8] በዚህ ዘመን ሥነ ጽሑፍ መርከቡ የጠፋበት መርከበኛ ተረት ፑንትን ይጠቅሳል።
- 1478 ዓክልበ. ግድም - ንግሥት ሃትሸፕሱት ቋሚ የንግድ መርከቦች ኃይል አሠራች።[9] በመቃብርዋ ግድግዳ የአምሥት መርከቦች ጉዞ ይዘገባል።[10] የሃትሸፕሱት ተልእኮ ኔህሲ በፑንት ሲደርስ የፑንት መሪዎች ንጉሥ ፓራሁ እና ንግሥት አቲ[11] ሰላምታ ሰጡት።[10]«ፑንት» የሚለው ሥያሜ በግብጽኛ ከጥንታዊ መንግሥት መዝገቦች ከ1500 ዓመታት በፊት የተወረሰ ነበር እንጂ ኗሪዎቹ ያንጊዜ አገራቸውን «ፑንት» እንዳሉት አይሆንም። ግብጻውያን ዕጣን፣ ቆጲ፣ ከብት፣ ዝሆን ጥርስ ወዘተ. ከፑንት ገዙ።[12]
- የሃትሸፕሱት ተከታዮች 3 ቱትሞሲስና 3 አመንሆተፕ ደግሞ የፑንት ንግድ አከታተሉ።[13]
- እስከ 1150 ዓክልበ. ግድም ድረስ በ3 ራሜሰስ ዘመን የፑንት ጉዞ ይዘገባል።[14]
Remove ads
ሥፍራ
ከፑንት የተገኙት አውሬዎች ቀጭኔ፣ አንኮ፣ ጉማሬ እና ነብር ስለ ሆኑ፣ ከዚያም በላይ የንግድ ዕቃ ዞጲ እና የዝሆን ጥርስ ሆኖ፣ አብዛኛው ሊቃውንት ፑንት በተለይ በአፍሪቃዊው ዳርቻ ላይ መሆኑን ያስቡታል።[15][16][17][18]
ከፑንት የደረሰ አንድ የአንኮ አስካሬን ቅርስ በግብጽ ተገኝቶ፣ በ2002 ዓ.ም. ሊቃውንት የጄኔቲክ ምርመራ አድርገው አንኮው በተለይ ከኤርትራና ኢትዮጵያ አንኮዎች ጋራ እንደ ተዘመደ አስታወቁ።[19]
![]() «ፕወነት» በግብጽኛ አጻጻፍ |
የፑንት ጎጆ በግድግዳ እንደ ተቀረጸ |
![]() የፑንት ጎጆዎች - ዘመናዊ አስተያየት |
ዋቢ ምንጮች
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads