3 መንቱሆተፕ
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
3 መንቱሆተፕ ሳንኽካሬ ግብጽን ከጤቤስ (11ኛው ሥርወ መንግሥት) የገዛ ፈርዖን ነበረ።

በሥነ ቅርስ ጉድለት ብዙ ስለ ፫ መንቱሆተፕ ድርጊቶች አይታወቅም። አንዳንድ ሕንፃ ከማሠራታቸው በላይ በተለይ የሚታወቀው በ2003 ዓክልበ. ግድም ወደ ፑንት አገር ለንግድ የላከው ተልእኮ ስለ ተከሠተ ነው። በአንድ ጽሑፍ ዘንድ ዓለቃው ሄኔኑና ፫ ሺህ ተጓዦች በየብስ እስከ ኮፕቶስ ከዚያም በመርከብ እስከ ፑንት ድረስ ሔዱ። ይህ ምናልባት የዛሬው ሶማሊላንድ ዙሪያ ይሆናል። ዕጣን፣ ሙጫ እና ሽቶ ይዘው ወደ ግብጽ ተመለሡ።
በ2002 ዓክልበ. ግድም በሞተበት ዓመት ልጁ 4 መንቱሆተፕ (ነብታዊሬ) ፈርዖን እንደ ሆነ ይታስባል።
ቀዳሚው 3 አንተፍ |
የግብፅ ፈርዖን | ተከታይ 4 መንቱሆተፕ |
Remove ads
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads