ማርክሲስም-ሌኒኒስም በተለይ በካርል ማርክስና በቭላዲሚር ሌኒን ትምህርት የተመሠረተ ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ነው።

ማርክሲስም-ሌኒኒስም የአንዳንድ መንግሥት ፍልስፍና በመሆኑ፣ በሃይማኖት ፈንታ እንደ የመንግሥት ሃይማኖት ያህል ያለ ሚና አጫውቷል።

Thumb
በአሁኑ ሰዓት (2010 ዓም) ማርክሲስት ወይም ኰሙኒስት የሆኑት አገራት

በአሁኑ ሰዓት በይፋ የማርክሲስት-ሌኒኒስት መንግሥት ያላቸው አገራት የሚከተሉ ናቸው፦

  • ቬትናም - ከ1937 ዓም ጀምሮ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1982 ዓም ይፋዊው ርዕዮተ ዓለም «የሆ ቺ ሚን ሃሣብ» ተብሏል።
  • የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ - ከ1941 ዓም ጀምሮ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1970 ዓም ይፋዊው ርዕዮተ ዓለም «ሶሻሊስም ከቻይናዊ ጸባይ ጋራ» ተብሏል።
  • ኩባ - ከ1951 ዓም ጀምሮ ርዕዮተ ዓለሙ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ሆኗል።
  • ላዎስ - ከ1967 ዓም ጀምሮ ርዕዮተ ዓለሙ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ሆኗል።
  • ስሜን ኮርያ - ከ1937 እስከ 1983 ዓም ድረስ በይፋ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1964 ዓም ጀምሮ ከማርክሲስም የተደረጀው ርዕዮተ ዓለም «ጁቼ» ኰሙኒስም ተብሏል። በ1983 ዓም ደግሞ «ማርክሲስም» በይፋ ተተወ።

ርስት ሁሉ የመንግሥት መሆኑ እንጂ የግል ርስት አለመኖሩ የሚገኝበት ሁናቴ የጀርመን ፋላስፋ የካርል ማርክስ ፍልስፍና ውጤት ነው። በተጨማሪ ማርክስ የሃይማኖት ወዳጅ ባለመሆኑ መጠን፣ ባለፈው ጊዜ በማርክሲስም-ሌኒኒስም በተገዙት አያሌ አገራት ውስጥ የሃይማኖት ወይም የኅሊና ነጻነት አልተገኘም።

በካርል ማርክስም ፍልስፍና ዘንድ ማንም ሕዝብ እንዳይበልጽጉ መቆጣጠር የመንግሥት ኃላፊነት ነው፣ ስለዚህ «ለሴ ፈር» ከ«ካፒታሊዝም» ጽንሰ ሀሣብ ጋር ይዘመዳል።

በቬትናም

በቻይና

ቻይና ከ1941 ዓም ጀምሮ ማርክሲስት ሲሆን ርዕዮተ አለሙ በይፋ «የማው ፀ-ቶንግ ሃሣብ» (ማዊስም) ነበር። በ1970 ዓም ወደ «ሶሻሊዝም ከቻይናዊ ጸባይ ጋር» ተቀየረ። በተጨማሪ «ሕዝብ እንዳይበልጽጉ» የሚለውን የማርክስ ጽንሰ ሀሣብ ትተዋል። የቻይና መሪ ደንግ ሥያውፒንግ በ1976 ዓም እንዳለ፣ «ሶሻሊስም ማለት ደህነትን ማጥፋት ማለት ነው።»

በኩባ

በላዎስ

ስሜን ኮርያ

ባለፈው ጊዜ

Thumb
በኰሙኒስም ጫፍ (1971-1976 ዓም) ማርክሲስት የነበሩት አገራት

የካርል ማርክስና የሌኒን ርዕዮተ ዓለም ቀድሞ ባለፈው ክፍለ ዘመን በበርካታ አገራት ተስፋፍቶ ነበር። ይህም ሁልጊዜ በአብዮትና በብሔራዊ ጦርነት ነበር።

በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግሥት በደርግ ዘመን (1966-1983 ዓም) በይፋ ማርክሲስት-ሌኒኒስት / ኰሙኒስት ነበረ።

ኢሕአዴግ መንግሥት (1983-2012 ዓም) ይፋዊ ርዕዮተ ዓለም «አብዮታዊ ዴሞክራሲ» ደግሞ በከፊል ከማርክሲስም-ሌኒኒስም የተደረጀ ሲሆን አንዳንድ የማርክስና በተለይም የሌኒን ተጽእኖዎች ቀርተው ነበር፤ ነገር ግን ከ1983 ዓም ጀምሮ በይፋ ርዕዮተ አለሙ ማርክሲስም / ኰሙኒስም አልነበረም። ከ2012 ዓም ጀምሮ ግን የአሁኑ መንግሥት ርዕዮተ አለም ለብልጽግና መደመር ነው።

[[መደብ:ሶሺያሊዝም

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.