ኅዳር ፲፭ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፸፭ኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፺፩ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፺ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

፲፱፻፶፮ ዓ.ም. ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን ገድለሃል ተብሎ የተወነጀለው ሊ ሃርቪ ኦዝዋልድ ዳላስ የፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞችና ቴሌቪዝን ድርጊቱን ለዓለም እየሰራጩ ሳሉ፤ ጃክ ሩቢ የሚባለው ሰው ኦዝዋልድን በሽጉጥ ገደለው።

፲፱፻፶፰ ዓ.ም. አምባገነኑ ጆሴፍ ዴዚሬ ሞቡቱኮንጎ የመሪነትን ሥልጣን በጉልበት ጨበጠ። በ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. የአገሪቱን ስም ቀይሮ ዛይር ተባለች። እሱም በአምባገነነንነት ሠላሣ ሁለት ዓመታት ከገዛ በኋላ በ፲፱፻፺ ዓ.ም. በኃይል ከሥልጣን ተወገደ።

፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ዶናልድ ዮሃንሰን እና ቶም ግሬይ አፋር ክልል ውስጥ ከ ሦሥት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ዓመታት በፊት የኖረችውን የድንቅነሽን ዓጽም አገኙ።

፲፱፻፸፰ ዓ.ም. የግብጽ ወታደራዊ ፈጥኖ ደራሽ ቡድን ተጠልፎ ማልታ ደሴት ላይ ከነመንገደኞቹ በጠላፊዎቹ ቁጥጥር ስር የነበረውን የዓየር ተሽከርካሪ ሲያስለቅቁ ሃምሣ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።

ልደት


ዕለተ ሞት

፲፱፻፶፮ ዓ.ም. – ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲን ገድለሃል ተብሎ የተወነጀለው ሊ ሃርቪ ኦዝዋልድ

ዋቢ ምንጮች

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.