![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/e/eb/Indo-European_branches_map.svg/langam-640px-Indo-European_branches_map.svg.png&w=640&q=50)
ህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ
From Wikipedia, the free encyclopedia
የህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ከአውሮፓና ከእስያ የሚገኝ ታላቅ የቋንቋዎች ቤተሠብ ነው።
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/e/eb/Indo-European_branches_map.svg/320px-Indo-European_branches_map.svg.png)
ከ2ኛ ዓለማዊ ጦርነት በፊት፣ በአንዳንድ የአውሮፓ ሊቃውንት ዘንድ እነዚህ ታሪካዊ በማይሆን አጠራር «የአርያኖች ቋንቋዎች» ይባሉ ነበር። እንዲያውም ግን «አርያን» የሚለው የብሔር ስም ከህንዳዊ-አራናዊ ቅርንጫፍ ውጭ አልታየም።
የቤተሠቡ ዋና ቅርንጫፎችና ልሳናት የሚከተሉ ናቸው። («*» ከአሁን በፊት ጠፍቷል ማለት ነው።)
- አናቶላዊ ቋንቋዎች *
- ኬጥኛ *
- ሉዊኛ *
- ቶኻርኛ ቋንቋዎች *
- ቶኻርኛ ሀ *
- ቶኻርኛ ለ *
- ጀርመናዊ ቋንቋዎች
- ኢታላዊ ቋንቋዎች
- ኬልታዊ ቋንቋዎች
- አርሜንኛ
- ባልቶ-ስላቫዊ ቋንቋዎች
- ግሪክኛ
- ህንዳዊ-ኢራናዊ ቋንቋዎች
- አልባንኛ
![](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/d/de/Globe_of_letters.svg/35px-Globe_of_letters.svg.png)