ሥነ-ፍጥረት
ሰው ከምን ተፈጠረ From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ሥነ-ፍጥረት ማለት ልዑል እግዚአብሔር በእውቀቱ ሰማይን፣ ምድርን፣ እንዲሁም በእነርሱ ውስጥ የሚገኙትን ሁሉ ከምንም ወይም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ብቁ ንቁ የሆኑ ሥነ-ፍጥረት የፈጠረበትን ሁኔታና ሥርዓት የምንማርበት ትምህርት ነው፡፡ ሥነ-ፍጥረት ማለት የፍጥረት መበጀት ማለት ነው፡፡ ይህ የሚታየው ዓለምና በውስጡ ያለው ሁሉ ከዚህ የሚታየው ዓለም ውጭም ያለው የማይታይ ዓለምና በውስጡ ያሉት ረቂቃን ፍጥረታት ሁሉ በእግዚአብሔር ተፈጥረዋል፡፡ /ዘፍ.1፣1 መዝ.101፣25 ኢሳ.66፣1-2 ዕብ.11፣3/ እግዚአብሔር ግዙፉንና ረቂቁን ዓለም የፈጠረው ከምንም ተነስቶ የሚያግናኛቸውና የሚያዋህደው ነገር ሳይኖረው/እምኀበ አልቦ/ ነው፡፡ /መዝ.32፣9 2ኛ መቃ.14፣10 ጥበብ.11፣18 የሐ.ሥራ 17፣24 ዕብ.11፣3 መዝ.148፣5
- እግዚአብሔር ፍጥረታትን የፈጠረው ሰውንና መላእክትን ስሙን ለመቀደስ ክብሩን ለመውረስ ሲሆን የተቀሩትን ፍጥረታት ግን ለአንክሮ ለተዘክሮ ለምግበ ስጋ ለምግበ ነፍስ ነው። /መዝ.148፣1-3 ራዕ4፣11 የሐ.ሥራ14፣17 ሮሜ.1፣20/
- እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ ፈጥሮ ያከናወነው በስድስት ቀናት ውስጥ ነው፡፡ /ዘፍ2 እና ዘጸ.20፣9-11/ በእነዚሀ ቀናት የተፈጠሩት ፍጥረታት እያንዳንዳቸው ቢቆጠሩ ፍጡር ተናግሮ አይፈጽመውም ነበር፡፡ ነገር ግን በባሕርያቸው በአኗኗራቸው በ22 ይመደባሉ፡፡ ኩፋሌ 3፣9 የተፈጠሩትም በሦስት መንገድ ነው፡፡ ይኸውም፡-
- በዝምታ /በአርምሞ/
- በመናገር /በነቢብ/
- በመስራት /በገቢር/ ናቸው፡፡
- ይህ መጣጥፍ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ነው። ስለ ፊዚክስ ለመረዳት የተፈጥሮ ሕግጋት ጥናትን ይዩ።
Remove ads
ፍጥረታት የተገኙበት ሁኔታ በሁለት ሁኔታ ነው፡፡ እነርሱም እምኸኀበ አልቦ አልቦ ኀበቦ (ካለመኖር ወደመኖር) በማምጣት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ግብር እም ግብር ከተፈጠሩት ላይ በመፍጠር ነው፡፡
- እምኀበ አልቦ ኀበቦ(ካለመኖር ወደ መኖር) በማምጣት የፈጠራቸው ፍጥረታት አራቱ ባሕርያት ማለትም ነፋስ ፣ እሳት ፣ውሃና መሬት ፣ ጨለማና መላእክት ናቸው፡፡
- ግብር እም ግብር (ከተፈጠሩት ላይ በመፍጠር) የተፈጠሩት ደግሞ ሌሎቹ ፍጥረታት ናቸው፡፡ መገኛቸውም አራቱ ባሕርያተ ስጋ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ እነሱን በማዋሐድ ፈጥሯቸዋል፡፡
ፍጥረታት የተገኙበት መንገድ ደግሞ ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም፡-
Remove ads
የእለተ እሑድ ፍጥረታት፡- እሑድ ማለት አሐደ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን የመጀመሪያ አንደኛ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ቀን ስምንት ፍጥረታትን እምኀበ አልቦ ኀበቦ አምጥቶ እሳት፣ ነፋስ፣ ውሃ፣ አፈር/መሬት፣ ጨለማ፣ ሰማያት፣ መላእከት እና ብርሃን ናቸው፡፡ /ዘፍ.1፣1 እሳት፣ ነፋስ፣ ውሃና መሬት አራቱ ባሕርያተ ስጋ ይባላሉ፡፡ ሰማያት ሰባት ናቸው፡፡ /መዝ.18፣1 ማቴ.3፣17 2ኛ ቆሮ.123 ዮሐ.14፣2 ዕዝራ ሱቱኤል 4፣4/
- ጽርሐ አርያም፡- ከሰማያት ሁሉ በላይ ናት፡፡ ለመንበረ መንግስት እንደ ጠፈር የምታገለግል ናት፡፡
- መንበረ መንግስት /መንበረ ስብሐት/፡- እግዚአብሔር በወደደው ምሳሌ ለፍጡራን የሚታይበት ነው፡፡ ለኢሳይያስ ለሕዝቅኤል ለወንጌላዊው ዮሐንስ በአምሳለ ንጉስ ታየቷቸዋል፡፡ ኢሳ.6፣1 ሕዝ.12፣6 ራዕ.4፣2 መዝ.10፣4 ሰማይ ውዱድን እንደ መሰረት አድርጎ ሰርቷታል፡፡
- ሰማይ ውዱድ፡- ከኪሩቤል ላይ ተዘርግቶ ለመንበረ መንግስት እንደ አዳራሽ ወለል ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡
- ኢየሩሳሌም ሰማያዊት፡- በፊት ሳጥናኤል የተፈጠረበት ኋላ የወጣባት ናት፡፡ ራዕ.12፣9 ይሁ.1፣6 በእለት ምጽአት በጎ የሰሩ ሰዎች የሚወርሷት የክርስቲያኖች ርስት ናት፡፡ ገላ.4፣4-26 ዕብ.12፣22 ዮሐ.14፣2 አስራ ሁለት ደጅ አላት፡፡ የደጆቿም ብርሃን ለዓይን እጅግ የሚስቡ ናቸው፡፡ የብርሃን መጋረጃም አላት፡፡ የ12ቱ ሐዋርያቱም ስም በመሰረቶቿ ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ በዚህም ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እግዚአብሔር የብርሃን ታቦትን ፈጥሮ አኑሮባታል፡፡ የአምላክ ማደሪያ የሆነች ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፡፡ /ራዕ.11፣19/
- ኢዮር
- ራማ
- ኤረር፤ እነዚህ ሦስቱ ዓለመ መላእክት /የመላእክት መኖሪያ/ ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በ3 ክፍል የምትሰራው በዚህ ምሳሌ ነው፡፡
Remove ads
መላእክት የተፈጠሩ በመጀመሪያ ቀን በእለተ እሑድ ነው፡፡ /ኩፋ.2፣6-8 በነገድ መቶ በከተማ አስር ነበሩ፡፡ መላእክት እምኀበ አልቦ ወይም ከአምላካዊ ብርሃን ተፈጥረዋል፡፡ አክሲማሮስ የተባለ መጽሐፍ መላእክት ከነፋስ ከእሳት ተፈጥረው ቢሆኑ እንደኛ ሞተው በፈረሱ በበሰበሱ ነበር ብሏል፡፡ በቅዱሳት መጽሐፍት በግብራቸው በእሳትና በነፋስ ተመስለዋል፡፡ መዝ.103፣4 ዕብ.1፣7 በእሳትና በነፋስ መመሰላቸው ነፋስ ፈጣን ነው መላእክትም ለተልእኮ ይፈጥናሉና፡፡ ነፋስ ረቂቅ ነው መላእክትም ረቂቃን ናቸው፡፡ እሳት ብሩህ ነው መላእክትም ብሩኀነ አእምሮ ናቸው፡፡ የመላእክት ባሕርይ ፦
- ስራቸው እግዚአብሔርን ያለ እረፍት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ሌትና ቀን ማመስገን ነው፡፡ /ኢሳ.6፣3 ራዕ.4፣8/
- መላእክት ከእግዚአብሔር ወደ ሰው ለምህረትና ለብስራታ ለቁጣም ይላካሉ፡፡ /ሉቃ.1፣1-26 ዘፍ.19፣1-38፤ 2 ነገሥ.19፣35…/
- ድኀነት የሚገባቸውን ሰዎች ይጠብቃሉ /መዝ.33፣7 90፣15/ ማቴ.18፣10 የሐ.ሥራ 12፣7/
- ክፉዎችን ይቃወማሉ፡፡ የሐሰትና የዓመጸኛ የክህደት ምንጭና አባት የሆነውን ዲያብሎስን /ሄኖክ.12፣3 መቅ.ወንጌል ራእይ. 13፣5 ዮሐ. 8፣44/ በመጀመሪያ የተቃወሙት መላእክት ናቸው፡፡ /ራዕ.12፣7/
- የቅዱሳንን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳረጋሉ፡፡ /ራዕ.8፣2-4 ጦቢ.12፣15/
- መላእክት ሰውን ያማልደሉ፡፡ ሰው ከፈጣሪው ጋር እንዲታረቅ ይጸልያሉ፡፡ የእግዚአብሔር ባለሟሎች ናቸውና ስለ ሰው ይለምናሉ፡፡ [1]
- መላእክት ሰውን ይረዳሉ፡፡ /ዘፍ 16፣7 21፣17፤ 1 ነገሥ.19፣5-7/ ሰውን ይጠብቃሉ፡፡ ለእያንዳንዱ ሰው ሁለት ጠባቂዎች አሉት፡፡ አንዱ መላእክ ቀን አንዱ ደግሞ ሌሊት ይጠብቁታል፡፡ /ማቴ.18፣10/
- የእግዚአብሔር አገልጋዮችን በችግራቸው ጊዜ ይረዳሉ ያበረታሉ፡፡ /የሐዋ.5፣12-24 12፣1-17 27፣22-25/
- መላእክት ንስሃ በሚገቡ ሰዎች ደስ ይሰኛሉ፡፡ /ሉቃ.15፣10/
- መላእክት ይህን የመስላሉ ቁመታቸው ይህን ያህላል ማለት አይቻልም ፡ ረቂቃን ናቸውና ሊያድኑ ያሉትን ለመታደግ በወጣትና በሽማግሌ በተለያዩ አምሳላት ይታያሉ፡፡
Remove ads
ሰኞ ማለት ሰኑይ ከሚለው የግእዝ ቃል የመጣ ሲሆን በሁለተኛው ቀን እግዚአብሔር ከምድር እስከ ብሩህ ሰማይ ሞልቶ የነበረውን ውኃ ወደ ላይና ወደ ታች ከፈለ፡፡ በመካከሉም ጠፈርን አደረገ፡፡ ጠፈርንም ሰማይ ብሎ ጠራው፡፡ ከጠፈር በላይ የተቀረውም ውኃ ሐኖስ ይባላል፡፡ ዘፍ.1፣6-8 ኩፋ.2፣9 የጠፈር ጥቅም፦
Remove ads
ማክሰኞ የሚለው ቃል ሠሉስ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ሦሥትኛ ቀን ማለት ነው፡፡ ፍጥረታት ከተፈጠሩ ሦስተኛ ቀን ነውና ሌላው ደግሞ ማክሰኞ የሚለው ቃል ማግሰኞ (የሰኞ ማግስት) ማለት ነው፡፡ በዚህ ቀን እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ ብሎ ውኃን ከመሬት ለይቶ ባህር ካለው በኋላ ሦስት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ ዘፍ. 1፣9-13 ኩፋ.2፣10-12፡፡ እነርሱም ፡- እጽዋት፣ አዝእርት፣ አትክልት ናቸው፡፡
- በምሳር የሚቆረጡ እጽዋት /ዛፎች/፡፡
- በማጭድ ሚታጨዱ አዝርዕት፡፡
- በእጁ የሚለቀሙ አትክልት ናቸው፡፡
- የገነት ተክል
ዕፅዋት አዝርእትና አትክልት ከአራቱ ባሕርያት ከመሬት ከውኃ ከነፋስ እና ከእሳት ተፈጥረዋል ይኸውም በግብራቸው ይታወቃሉ፡፡ የዚህ እለት ፍጥረታት ለምስጢረ ስጋዌ ምሳሌ እንጠቀምበታለን፡፡
Remove ads
ሥነ-ፍጥረት እለት ረቡእ ራብዕ ከሚለው የግእዝ ቃል የመጣ ሲሆን አራተኛ ቀን ማለት ነው፡፡ ሥነ ፍጥረታት ከተፈጠሩ አራተኛ ቀን ማለት፡፡ በእለተ ረቡዕ ሦስት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ እነዚህም፡- ፀሐይ ጨረቃና ከዋክብት ናቸው። /ዘፍ.1፣14-16/ ከዋክብትና ጨረቃን በሌሊት ፀሐይን በቀን አሰለጠናቸው /መዝ.135፣8-9/። ፀሐይ ከእሳትና ከነፋስ በመፈጠሯ ትሞቃለች ትሄዳለች፡፡
ጨረቃና ከዋክብት የተፈጠሩት ከነፋስና ከውኃ ነው፡፡ ከነፋስ በመፈጠራቸው ይሄዳሉ፣ ከውኃ እንደመፈጠራቸው ደግሞ ይቀዘቅዛሉ፡፡ እነዚህንም ለዕለታት ለሳምንታት ለወራት ለአመታትና ለክፍለ ዘመናት መታወቂያ መለያ እንዲሆኑ ፈጥሮአቸዋል /ኩፋ.2፣13-14/፡፡ የዚህ እለት ፍጥረታት ለምስጢረ ትንሳኤ ሙታን ምሳሌ እንጠቀምባቸዋለን፡፡
Remove ads
ሐሙስ የሚለው ቃል ሃምሳይ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን አምሰተኛ ቀን ማለት ነው፡፡ አምስተኛ መባሉም ፍጥረታት ከተፈጠሩ አምስተኛ ቀን ሆኗልና፡፡ በእለተ ሐሙስ ሦስት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ በልብ በሚሳቡ፣ በእግር የሚሽከረከሩ በክንፍ የሚበሩ በባህር ተወስነው የሚኖሩ በደመ ነፍስ ሕይወት ሕያዋን የሆነ ፍጥረታትን ፈጠረ። /ዘፍ.1፣20-23 ኩፋሌ.2፣15-16 እነዚህም ዘመደ እንስሳ፣ ዘመደ አራዊት፣ ዘመደ አእዋፋት ይባላሉ፡፡
አርብ ማለት አርበ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን አካተተ ፈጸመ ማለት ነው፡፡ በእለተ አርብ እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረታትን ፈጥሮ ጨርሷልና በዚህ ቀን እግዚአብሔር አራት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ እነርሱም በእግር የሚሽከረከሩ በክንፍ የሚበሩና በልብ የሚሳቡ በየብስ የሚኖሩ በደመ ነፍስ ሕይወት ሕያዋን የሆኑ ፍጥረታትን ፈጠሩ፡፡ በመጨረሻም አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ሰውን በመልካችን እንፍጠር ብለው ዓርብ እለት በነግህ አራቱን ባሕርያተ ሥጋ አምስተኛ ባሕርየ ነፍስን አዋህደው የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ አድርጎ በማዕከለ ምድር /መዝ.73፣12/ በቀራኒዮ አዳምን ፈጠሩት፡፡
- እንስሳት፡- ሳር ነጭተው ውኃ ተጎንጭተው የሚኖሩ
- አራዊት፡- ሥጋ በጭቀው ደም ተጎናጭተው ውኃ ጠትተው የሚኖሩ
- አዕዋፋት፡- የዛፍ የእህልን ፍሬ ለቅመው ሥጋ በልተው ውኃ ጠጥተው የሚኖሩ ናቸው፡፡
አዳም ማለት ይህ ቀረው የማይባል ያማረ መልከ መልካም ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ከመሬት መፈጠሩን ያመለክታል፡፡ ሰው አራት ባሕርያተ ስጋ አምስተኛ ግብራተ ነፍስ አሉት፡፡
- የነፍስ ግብራት፡- ልባዊነት፣ ነባቢነት፣ ሕያውነት
- ባሕርያተ ሥጋ፡- ውኃ፣ መሬት፣ ንፋስና እሳት
አዳም በተፈጠረ በሳምንቱ ጠዋት ሦስት ሰዓት ሲሆን «አዳም ብቻውን የሆን ዘንድ አይገባውም የምትመቸውን እረዳት እንፈጠርለት» ብሎ ወዲያውኑ በአዳም እንቅልፍ አመጣበት ከአዳም ጎን አንዲት አጥንት ወስዶ ለአዳም ምትረዳውን ሴት ፈጠረለት ዘፍ.2፣18-23 ኩፋ.4፣4። እግዚአብሔር ሔዋንን ከጎኑ ፈጥሮ ባሳየው ጊዜ አዳም «ይህች አጥንት ከአጥንቴ የተገኘች ናት ሥጋዋም ከስጋዬ የተገኘች ናትና ሴት ትባል» አለ (ዘፍ.2፣23)። ሕይዋን ማለት የሕያዋን ሁል እናት ማለት ነው፡፡ ዘፍ.3፣20 ሕይዋን ከጎኑ መፈጠሯ ወንድና ሴት (ባልና ሚስት) አንድ አካል መሆናቸውና የሰው ዘር ሁሉ ከአንድ ግንድ መገኘቱን ያመለክታል፡፡ ሔዋንን ስለ ሦስት ነገር ፈጥሮታል፦
- ረዳት እንድትሆን
- ዘር ለመተካት
- ከፍትወት ለመጠበቅ
ሰው ከፍጥረታት ሁሉ የከበረ ነው፡፡ (መዝ.48 ፣12) ይኸውም የሚታወቀው፦
- ፍጥረታት ሁሉ ከተፈጠሩ በኋላ በመፈጠሩ
- በእግዚአብሔር አራያና አምሳል በመፈጠሩ
- በምድር ላይ የሚኖሩ ፍጥረታት በሙሉ ገዥ አዛዥ ሆኖ በመፈጠሩ
22ቱ ሥነ-ፍጥረት የሚባሉት እነዚህ ከላይ ያየናቸው ናቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ቅዳሜ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ ፈጥሮ ከስራው አረፈ፡፡ ስለዚህ ይህች ዕለት ሰንበት ሆና እንድትከበር ሥጋዊ ስራዎች እነዳይሰሩባት የእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ሆነ፡፡ ይኸውም እግዚአብሔር ከስራው ሁሉ አርፎባታልና ነው /ዘፍ.2፣2/፡፡
ደግሞ ይዩ
reference
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads