የላሊበላ ከፍልፍል ድንጋይ የተሠሩ አብያተ ክርስቲያናት
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
በአጭሩ ስለ ዓለት ላይ የተሠሩ አብያተ ክርስቲያናት፣ የዛጉዌ ነገስታት ከሚታወቁባቸው ዓበይት ነገሮች አንዱና ዋነኛው ከተፈጥሮ ዋሻ ውስጥ በመገንባትና ከዓለት ላይ በመፈልፈል አብያተ ክርስቲናትን ማነጻቸው ነው፡፡
ንግስናን ለይሁዳ(አማራ (ከ12ቱ የስራዔል ነገዶች አንዱ) መዳንን ለአሮን እንደተሰጠ ሁሉ ሹም የሚል ስልጣን ደግሞ ለአገው ተሠጥቷል። አማራ ከዳማት ተነስቶ አክሱምን ያጸና፣ ከአክሱም ተነሥቶ ዛግዊን የመሰረተ ፣ ከዛግዌ ተነስቶ ሰለሞናዊ ስርዎ መንግስትን መስርቶ የንግስና ስርዓትን አስቀጥሏል። አማራ የጥንት የኢትዮጵያ መስራች ሲሆን በሒደት ከአገው ጋር ተጋብቶ የተቀላቀለ ህዝብ ስለሆነ አገው አማራ ነው ወደ ማለት ተደርሷል።
እንዲህ ዓይነቱ ሥራ የተጀመረው በ6ኛው መ/ክ/ዘ በአፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት ቢሆንም ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የላቀ ደረጃ የደረሰው ግን በዛጉዌ ነገሥታት ነው፡፡ ለዓለም አስደናቂ ሆኖ የተሠራው ግን በንጉሥ ላሊበላ ነው:: በዚህ ዘመን ከዋሻ ውስጥና ከውቅር አለት አብያተ ክርስቲያናትን ማነፁ እንዲሁም ዝም ብሎ ሳይሆን ራሱን የቻለ ሃይማኖታዊ ትርጉምና መጽሐፍ ቅዱሳዊ አንድምታ ያለው ነው፡፡ ይህ ንጉሥ በጣም እግዚአብሔርን ወዳጅ ነበረ::
እንደሚታወቀው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው በቤቴልሄም ዋሻ ውስጥ ሲሆን የተቀበረው ደግሞ ዮሴፍ ለራሱ ጠርቦ ባዘጋጀው አዲስ መቃብር በጎለጎታ ነው፡፡ ስለሆነም አብያተ ክርስቲያናት ከዋሻ ውስጥ መሠራታቸው የጌታችንን የትውልድ ቦታ (የቤቴልሔም ዋሻ) ፣ ከውቅር ዓለት መታነጻቸው ደግሞ የጌታችንን የመቃብር ቦታ (ጎለጎታን) የሚያስታውሱን ናቸው ፣ ሌላም ብዙ ብዙ ትርጉም አላቸው
| ኢትዮጵያ | 
| 
 ታሪካዊ ቦታዎች  • አክሱም • ላሊበላ • ጎንደር • ነጋሽ • ሐረር • ደብረ-ዳሞ • አዲስ አበባ   | 
Remove ads
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads



