E
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
E / e በላቲን አልፋቤት አምስተኛው ፊደል ነው።
- (ለሥነ ሂሣብ ቁጥር፣ «ኦይለር ቁጥር» ያንብቡ።)

በእንግሊዝኛ የፊደሉ ስም አጠራር /ኢ/ ሲሆን፣ ይህ ታላቅ የአናባቢ መፈራረቅን ያንጸባርቃል። ባብዛኛው ቋንቋዎች ግን በተለመደው የአናባቢ «ኤ» ን ድምጽ ኃይል ይወክላል።
የ«E» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ሄ» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የሚደሰት ሰው ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ።
በፊንቄ ጽሕፈት የፊደሉ ድምጽ እንደ ተናባቢ («ህ») ሲሆን በግሪክ አልፋቤት ግን ይህ ምልክት የአናባቢ ድምጽ «ኧ» ለማመልከት ተጠቀመ። አሁን በዘመናዊ ግሪክ ይህ ፊደል (Ε ε) «ኧፕሲሎን» (ከ«ኧ ፕሲሎን» ወይም «ቀላል ኧ») ይባላል።
በግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ሀ» («ሆይ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ሄ» ስለ መጣ፣ የላቲን 'E' ዘመድ ሊባል ይችላል።
Remove ads
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads