መስከረም ፲፰
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፲፰ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፫፻፵፰ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ማቴዎስ እና ማርቆስ ደግሞ ፫፻፵፯ ዕለታት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- መስከረም ፲፰ ፩ሺ፫፻፵፪ ኤዎስጣጤዎስ ያረፉበት ቀን ፣ እንዲሁ ም የንግሣቸው ቀን።
- ፲፱፻፲፯ ዓ/ም - ሁለት የአሜሪካ የጦር አየር ዠበቦች፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለምን ዙሪያ በአየር በረራ በመቶ ሰባ አምሥት ቀን ካከናወኑ በኋላ ሲያትል ላይ አረፉ።
- ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - ዓለቃ እስክንድር ፍሌሚንግ (Sir Alexander Fleming) የተባለ ሰው ፔኒሲሊን አገኘ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - ማሊ እና ሴኔጋል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባላት ሆኑ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በአፍሪቃ አኅጉር ላይ የመጀመሪያውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ያካሄዱት የግብጽ ሁለተኛ ፕሬዚደንት የነበሩት ኮሎኔል ጋማል አብደል ናስር አረፉ።
- ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በሮማው የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር በፓፓነት የተመረጡት ቀዳማዊ ዮሐንስ ጳውሎስ በተመረቁ በ ሰላሳ ሦስት ቀናቸው ሞቱ።
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads