ኅዳር
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ኅዳር የወር ስም ሆኖ በጥቅምት ወር እና በታኅሣሥ ወር መሀከል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ ሦስተኛው የወር ስም ነው።
የኅዳር ቀናት | ||||||
1 | 2 | 3 | 4 | 5 | 6 | 7 |
8 | 9 | 10 | 11 | 12 | 13 | 14 |
15 | 16 | 17 | 18 | 19 | 20 | 21 |
22 | 23 | 24 | 25 | 26 | 27 | 28 |
29 | 30 |
«ኅዳር» ከግዕዙ «ኅደረ» ከሚለው ግስ የተባዛ ነው።[1] ይህም የሆነ፣ በዚህ ወር እረኞች ሰብላቸውን ለመጠብቅ ጎጆ በዱር ሠርተው ስለሚያድሩበት እንደ ሆነ ይባላል።[2]
በቅብጢ አቆጣጠር የዚህ ወር ስም ሐጦር ነው። ይህም በጥንታዊ ግብጽ አረመኔ ሃይማኖት ከጣኦት ስም «ሑት-ሔሩ» መጣ።
በጎርጎርዮስ አቆጣጠር የኖቬምበር መጨረሻና የዲሴምበር መጀመርያ ነው።
በኅዳር ወር ፲፱፻፲፩ ዓ/ም የቸነፈር (ግሪፕ) በሽታ በአዲስ አበባ እና በሌላውም የኢትዮጵያ ግዛት ላይ ተነስቶ በመዲናው ብቻ ከዓሥር ሺ በላይ ሰዎች ሞቱ።[3]። ይሄ በሽታ በዚያ ወቅት በዓለም ላይ ተሰራጭቶ የነበረው የ "እስፓኝ እንፍልዌንዛ በመባል የሚታወቀው የጉንፋን 'ወረርሽኝ' ነው።
Remove ads
በኅዳር ወር ነጻ የወጡ የአፍሪቃ አገሮች
ዘመን
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads