መስከረም ፰
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
መስከረም ፰ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፰ኛው ቀን ሲሆን የክረምት ወቅት ፸፱ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፶፰ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፶፯ቀናት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፫፻፹፯ዓ/ም - የሮማ ንጉዛት ክርስቲያናዊ ቄሳር ቀዳማዊ ቴዎዶስዮስ ዘውዱን ለመንጠቅ የተነሳውን አረመኔያዊ የምዕራብ ሮማ መሪ አውግንዮስን በፍሪጊዱስ ውግያ ሲያሸንፍ የሮማ ክርስቲያናዊ ንጉዛት በመጽናቱ የክርስትና ሃይማኖት በአውሮፓ ቀደምትነትን እንዲይዝ አድርጎታል።
- ፲፰፻፺፱ ዓ/ም - በሆንግ ኮንግ አካባቢ የተከሰተ አውሎ ንፋስ እና የባሕር ሞገድ (tsunami) ፲ ሺ የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት አጥፍቷል።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሁለተኛው ዋና ፀሐፊ፣ ሲዊድናዊው ዳግ ሀመርሾልድ በ’አየር ዠበብ አደጋ’ በቀድሞዋ ሮዴዚያ (የአሁኗ ዚምባብዌ) ላይ ሞቱ።
- ፳፻፬ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ባጸደቀው አዋጅ ቁጥር 654/2001 መሠረት በየዓመቱ በመስከረም ወር በሁለተኛው ሳምንት ዕለተ ሰኞ እንዲከበር በተወሰነው ድንጋጌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አርማ ያለበት ሰንደቅ ዓላማ ቀን።
Remove ads
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 31/165300 Ethiopia: Annual Review of 1961
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads