መጋቢት ፳፬
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
መጋቢት ፳፬፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፬ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፹፱ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፷፪ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፷፩ ቀናት ይቀራሉ።
- ፳፻፲ ዓ.ም. - ዶ/ር ዓቢይ ኣሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ።
- ፲፮፻፸፪ ዓ/ም - ድፍን የፀሐይ ጋረዶ በኢትዮጵያ ላይ አለፈ፣ ፀሐይ ጨለመች።
- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽና ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴ፣ ንጉሥ ተፈሪ መኮንን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተብለው በንጉሠ ነገሥት ዙፋን ተቀመጡ፡፡
- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ በነገሡ በአሥራ ሦሥት ዓመት ተኩል በ፶፬ ዓመት ዕድሜያቸው ዐረፉ። የሞታቸው ዜና እንደተሰማም በከተማው የሐዘን ጥላ አጠላበት። አባታቸው ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ በተቀበሩበት በታዕካ ነገሥት በዓታ ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ።
- ፲፱፻፺፯ ዓ/ም - የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ዳግማዊ አቡነ ዮሐንስ-ጳውሎስ በ፹፬ ዓመት ዕድሜያቸው አለፉ።
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትሪያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads