ግንቦት ፫

From Wikipedia, the free encyclopedia

Remove ads

ግንቦት ፫ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵፫ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፴፰ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፫ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፳፪ ቀናት ይቀራሉ።


ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፱፻፲፮ ዓ/ም - ሁለቱ ጀርመናውያን ተሽከርካሪ አምራቾች፣ ጎትሊብ ዴይምለር እና ካርል ቤንዝ ኩባንያዎቻቸውን አዋሕደው አዲሱን የመርሴዲስ-ቤንዝ (Mercedes-Benz) ኩባንያ መሠረቱ።
  • ፲፱፻፵፰ ዓ/ም- የብሪታኒያ የቅኝ ግዛቶች ሚኒስትር የምዕራብ አፍሪቃዋ ጎልድ ኮስት (በኋላ ጋና) ነጻነቷን እንደምትሰጥ መወሰኑን ለሕዝብ ተወካዮች ሸንጎ አስታወቀ።
  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ “የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጣልቃ ገቦች በአገሪቱ ጉዳይ ውስጥ እየገቡ አስቸግረዋል በሚል መነሻ የፈረንሳይን፤ አሜሪካን፤ ግብጽን፤ የሶቪዬት ሕብረትን፤ የብሪታኒያን እና የዩጎዝላቪያን የልዑካን አለቆች ሰብስበው አነጋገሩ። በማግሥቱ ይፋ የተደረገው ጽሑፋዊ ቃለ-ጉባኤ አምባሳደሮቹ የተጠሩት “የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ጉዳዮች ላይ የባዕዳንን ጣልቃ ገብነት በብርቱ እንደሚቃወም እና በኢትዮጵያ ግዛትና ሉዐላዊነት ላይ የሚሰነዘሩትን ማናቸውንም እርምጃዎች ለመከላከል ቆራጥ መሆኑን እንዲገነዘቡ ነው።” ይላል።
Remove ads

ልደት

ዕለተ ሞት

ዋቢ ምንጮች

  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 Annual Report from Ethiopia for 1960
  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660 ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1973


More information የኢትዮጵያ ወራት ...
Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads