መስከረም ፲፱
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፲፱ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፫፻፵፯ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ማቴዎስ እና ማርቆስ ደግሞ ፫፻፵፮ ዕለታት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
፲፱፻፴፮ ዓ/ም - የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጀመሪያ ላይ የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት አገራችንን ኢትዮጵያን ሲወር በድል አድራጊነት አዲስ አበባ የገባው ማርሻል ፒዬትሮ ባዶልዮ፤ ተሸናፊዋን አገሩን በመወከል የሽንፈቱን ስምምነት ፈረመ።
፲፱፻፶፫ ዓ/ም - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ከዚያ በፊት ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ በ ሶቪዬት ኅብረት መሪ ኒኪታ ክሩስቾቭ ድንፋታ ተረበሸ። በዚህ ስብሰባ ላይ ክሩስቾቭ ጫማቸውን አውልቀው ጠረጴዛቸውን በመቀጥቀጥ ዓለምን አስገርመዋታል።
፳፻፪ ዓ/ም - በሳሞዓ አጥቢያ የተከሰተው፣ በ ‘ሪክተር ሚዛን’ ስምንት ነጥብ ያስመዘገበው የመሬት እንቅጥቅጥ ‘ሱናሚ’ (tsunami) የሚባለውን የባሕር ነውጥ አስከተለ።
Remove ads
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads