መስከረም ፭

From Wikipedia, the free encyclopedia

Remove ads

ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፭ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፷፩ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፷ ዕለታት ይቀራሉ።

መስከረም ፭


ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፭፻፴፫ ዓ/ም -አጼ ልብነ ድንግል በነገሡ በ፴፪ ዓመታቸው ሐሙስ ዕለትደብረ ዳሞ ላይ አረፉ። የንጉሠ ነገሥትነት ሥልጣን፣ ዘውድና ዙፋናቸው በዚሁ ዕለት ወደልጃቸው የ ፲፰ ዓመቱ አጼ ገላውዴዎስ (ስመ መንግሥት፣ አፅራር ሰገድ)ተላለፈ።
  • ፳፻፫ ዓ/ም - በሁለት ትላልቅ የኢትዮጵያሕዝባዊ ድርጅቶች የመሪዎች መፈንቅል ተፈጸመ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ላለፉት ስድስት ዓመት ያገለገሉት አቶ ግርማ ዋቄ፣ ሥራቸውን ለቀቁ። አቶ ግርማን የሚተኳቸው ምክትላቸው አቶ ተወልደ ገብረማርያም ይሆናሉ ይባላል። በዚሁ ዕለት የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ላለፉት አራት ዓመታት ያገለገሉት አቶ አማረ አምሳሉም ሥራቸውን ለቀቁ
Remove ads

ልደት

  • ፲፰፻፹፫ ዓ/ም በወንጀላዊ ልብ ወለድ ጽሑፎቿ “አቻ የላት” የምትባለው እንግሊዛዊቷ ደራሲ አጋታ ክሪስቲ (Agatha Christie)፣ ቶርኪ (Torquay) በምትባል ከተማ ተወለደች። (ክሪስቲ በ ፲፱፻፷፰ ዓ/ም ሞተች)


ዕለተ ሞት

  • ፲፫፻፵፮ ዓ/ም - ኢትዮጵያዊው መነኩሴ አባ ኤውስጣቴዎስ በስደት በሚኖሩበት አርመን አገር ላይ ሞቱ።

ዋቢ ምንጮች



More information የኢትዮጵያ ወራት ...
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads