ዐይን (ፊደል)
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ዐ ዑ ዒ ዓ ዔ ዕ ዖ
ዐይን በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 16ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ በሶርያም ፊደሎች 16ኛው ፊደል «ዐይን» ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ዐይን» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 16ኛ ነው።
በመጀመርያው (ግዕዝ) ቅርጽ (አ) በልሳነ ግዕዝ እንደ ሌሎቹ ፊደላት የ«ኸ» አናባቢ ድምጽ ሆነው ነበር፤ በአማርኛ ግን ድምጹ እንደ አራተኛው (ራብዕ) ቅርጽ (ዓ) አንድላይ ነው። በአማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ ከአልፍ (አ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል። ቀድሞ ግን ድምጾቻቸው የተለያዩ ነበሩ።
Remove ads
ታሪክ
የዐይን መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የዐይን ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አጠራሩ ግን «ኢር» ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ዐይን» ስላሉት፣ ይህ ስዕል «ዐ» ሆኖ እንዲሰማ መጣ።
የከነዓን «ዐይን» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ የአረብኛም «ዐይን» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «ኦሚክሮን» (ትንሹ ኦ ማለት፣ Ο, ο) አባት ሆነ። እሱም የላቲን አልፋቤት (O o) እና የቂርሎስ አልፋቤት (О о) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«ዐይን» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር ፸ (ሳባ) ከግሪኩ ο በመወሰዱ እሱም የ«ዐ» ዘመድ ነው።
Remove ads
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads