የመን (ፊደል)
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
የ ዩ ዪ ያ ዬ ይ ዮ
የመን (ወይም የማን) በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ ዐሥረኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ በሶርያም ፊደሎች ዐሥረኛው ፊደል «ዮድ» ይባላል።
በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ያእ» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 10ኛ ነው። (በዘመናዊ ተራ ግን 28ኛው ነው።)
ታሪክ
የየመን መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የእጅ ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አጠራሩ ግን «ዐ» ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ዮድ» ስላሉት፣ ይህ ስዕል «ይ» ሆኖ እንዲሰማ መጣ። በግዕዝ ቃሉ «እድ» ሆኖ በዚሁ ድምጽ ስለማይጀመር፣ በ«ዮድ» ፈንታ የፊደል ስም «የመን» (ማለት ቀኝ እጅ) ይባላል።
የከነዓን «ዮድ» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ «ዮድ» የአረብኛም «ያእ» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «ኢዮታ» (Ι, ι) አባት ሆነ። እሱም የላቲን አልፋቤት (I i) እና (J j) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«የመን» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር ፲ (አሥር) ከግሪኩ ι በመወሰዱ እሱም የ«የ» ዘመድ ነው።
Remove ads
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads