ጠይት
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ጠ ጡ ጢ ጣ ጤ ጥ ጦ ጧ
ጠይት (ወይም ጣይት) በአቡጊዳ ተራ ዘጠነኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥና በሶርያ ፊደሎች ዘጠነኛው ፊደል "ጤት" ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል "ጣእ" ተብሎ በ"አብጃድ" ተራ 9ኛ ነው። (በዘመናዊ ተራ ግን 16ኛው ነው።)
በአማርኛ ደግሞ "ጨ ጩ ጪ ጫ ጬ ጭ ጮ" ከ"ጠ..." ትንሽ ተቀይሯል።
ታሪክ
የጠይት መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ቢታስብም እስካሁን አልተገኝም። በከነዓን ጽሕፈት ፊደሉ የመንኮራኩር ስዕል መስለ። ለዚህም ምናልባት ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ "ኒውት" ("መንደር") ነበር። አንዳንድ ሊቃውንት ግን ሌላ ስዕል "ጥሩ" ("ነፈር") እንደ ነበር ይገምታል።
የከነዓን "ጤት" የዕብራይስጥና የአራማያ "ጤት" የአረብኛም "ጣእ" ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት "ጤታ" (Θ, θ) አባት ሆነ። እነዚህ የ"ጠይት" ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር ፱ (ዘጠኝ) ከግሪኩ θ በመወሰዱ እሱም የ"ጠ" ዘመድ ነው።
Remove ads
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads