ግንቦት ፲፫
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ግንቦት ፲፫ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፶፫ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፵፰ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፲፫ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፲፪ ቀናት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የየካቲት ፲፪ ቀን አዲስ አበባ ላይ ግራዚያኒ ላይ የተወረወረውን ቦምብ ምክንያት በማድረግ ፋሺስቶች ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብተው ፫፻፳ መነኮሳትን በግፍ ጨፈጨፉ፤ ገዳሙንም አቃጠሉ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የአሩሲ ጠቅላይ ግዛት (አሁን አርሲ) እንደራሴ ሆነው የተሾሙትን አቶ ተስፋ ቡሸን የጠቅላይ ግዛቱ ሕዝብ አባሮ አስወጣቸው።
- ፲፱፻፹፫ ዓ/ም - የኢሕዲሪ (የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ) ፕሬዚዳንትና የኢሠፓ (የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ) ዋና ጸሐፊ የነበሩት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አገር ጥለው በመኮብለል ዚምባብዌ ገቡ።
- ፲፱፻፹፮ ዓ/ም - የየመን ሪፑብሊክ ውሕደት በተፈጸመ በአራት ዓመቱ ሁለቱ ወገኖች ባለመስማማታቸው በመኻላቸው የእርስ በእርስ ጦርነት ተጀመረ።
- ፲፱፻፺፭ ዓ/ም በሰሜናዊ አልጄሪያ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ ከሁለት ሺ በላይ ሰዎችን አጥፍቷል።
Remove ads
ልደት
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም በዚህ ዕለት አዲስ አበባ ተወለዱ።
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829 ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
- http://www.ethiopianreporter.com Archived ጃንዩዌሪ 24, 2005 at the Wayback Machine ኪንና ባህል፡ ሳምንቱ በታሪክ
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/May_21
Remove ads
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads