ግንቦት ፳፬

From Wikipedia, the free encyclopedia

Remove ads

ግንቦት ፳፬ ቀን

ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፷፬ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፻፪ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፩ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፯፻፹፬ ዓ/ም - ኬንታኪአሜሪካ መንግሥታት ኅብረት ፲፭ኛዋ አባል ሆነች።
  • ፲፯፻፹፰ ዓ/ም - ሚሲሲፒአሜሪካ መንግሥታት ኅብረት ፲፮ኛዋ አባል ሆነች።
  • ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በ፳ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በትልቅነቱ በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የሌለው በ”ሪክተር” ሚዛን ስድስት ነጥብ ሰባት ያስመዘገበ የመሬት እንቅጥቅጥ ተከስቶ የማጀቴን ከተማ ሲደመስስ፣ በጎረቤቷ ካራቆሬ ደግሞ ከመቶ እጅ አርባ አምሥቱ መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። ከካራቆሬ በስተሰሜን የሚያልፈው ዋናው የአዲስ አበባአስመራ መንገድ እና ድልድዮችም እንቅጥቅጡ ባስከተለው የድንጋይ ናዳ ወደ አሥራ ሰባት ኪሎ ሜትር ርዝመት ላይ አደጋ ደረሰ።
  • ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - ከዘጠኝ ወራት በኋላ ነጻነቷን የተቀዳጀችው ኬንያ፣ በዛሬው ዕለት እራሷን የማስተዳደር መብት ተፈቀደላት። ይሄንን ዕለት በየዓመቱ “የማንዳራካ ቀን” በሚል ስያሜ ኬንያ ታከብረዋለች።
  • ፲፱፻፸፩ ዓ/ም - በቀድሞዋ ሮዴዚያ (አሁን ዚምባብዌ) በ፺ ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቁሮች የሚመራ መንግሥት ሥልጣንን ጨበጠ።
  • ፲፱፻፸፪ ዓ/ም - ‘ሲ. ኤን. ኤን.’ (CNN) የተባለው የዜና ማሠራጫ ድርጅት ሥራውን ጀመረ።
  • ፲፱፻፺፫ ዓ/ም - የኔፓል አልጋ ወራሽ ልዑል ዲፔንድራ አባታቸውን ንጉሥ ቢሬንድራን፤ እናታቸውን ንግሥት አይስዋርያን እና ሌሎችንም ንጉሣዊ ቤተ ሰባቸውን ረሽነው ከገደሉ በኋላ እራሳቸውንም በጥይት አጠፉ።
Remove ads

ልደት


ዋቢ ምንጮች


More information የኢትዮጵያ ወራት ...
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads