ኅዳር ፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፷፪ኛው እና የመፀው ወቅት ፴፯ተኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፬ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፫ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፰፻፹፪ ዓ.ም. - በሰሜን ምዕራብ አሜሪካ የሚገኘው የዋሽንግተን ግዛት ከአሜሪካ ኅብረት ጋር በመወሐድ አርባ ሁለተኛው አካል ሆነ።
  • ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. - ከአራት ዓመት ጦርነት በኋላ የአንደኛው የዓለም ጦርነት በአንድ በኩል ንምሳ በሌላ በኩል ተቃዋሚዎቿ አባር አገሮች በስምምነትና በፊርማ ውጊያው ከጧቱ አምስት ሰዐት ላይ እንዲያቆም ተስማሙ። ይሄ ድርጊት በየዓመቱ ከጧቱ አምስት ሰዐት ላይ በሁለት ደቂቃ ሕሊናዊ ጸሎት ይከበራል።
  • ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. - በቀድሞዋ ሰሜን ሮዴዚያ፤ በዛሬይቷ ዚምባብዌ በነጩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኢያን ስሚዝ የሚመራው መንግሥት ከህግ ውጭ አገሪቱን ከብሪታንያ ነጻነት አወጀ።
  • ፲፱፻፺፯ ዓ.ም - የፍልስጥኤም ነጻነት ግንባርን እና የፍልስጥኤምን ሕዝብ ከአርባ ዓመት በላይ የመሩት ያሲር አራፋት በተወለዱ በሰባ አምሥት ዓመታቸው በፓሪስ ሆስፒታል አረፉ፡ ወዲያው ማህሙድ አባስ በእሳቸው ምትክ የድርጅቱ መሪ ሆነው ተመረጡ።

ልደት

  • ፲፰፻፷፪ ዓ.ም.- ፋሺስት ኢጣልያ አገራችንን ኢትዮጵያን በወረረበት ዘመን፤ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትነትን ሥልጣን ይዘው የነበሩት የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶር ኢማኑኤል ሣልሳዊ በዚህ ዕለት ተወለዱ።

ዕለተ ሞት


ዋቢ ምንጮች


More information የኢትዮጵያ ወራት ...
Close

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.